>

የሴራ ፖለቲካ ዶ/ር አብይን እንደ ሙርሲ (በድሉ ሌሊሳ)

የዶ/ር አብይን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ  በመከላከያና በመረጃ መረብ ደህንነት ተቋም ውስጥ ቁልፍ ስልጣን የነበራቸው ግለሰቦች ገለል መደረጋቸው ይታወቃል። እናም ያኮረፈ ቡድን ማድረግ የሚችለውን ነገር ከመሞከር እንደማያርፍ ግልፅ ነው። ሰሞኑን ሶማሌ ክልል አብዲ ኢሌ ላይ ተቃውሞ ተነሳ ተብሎ ፌ.ቡ ላይ ሲሽከረከር ቆየና መስፋት ሳይችል ይቀርና ይቆማል። እኔን ሲመስለኝ ተቃውሞው ከሶማሌ ክልል ይነሳ እንጂ አላማው ኦሮሚያ ላይ የተቃውሞ ቤዝ መስራት ይመስለኛል። ግምታችንን የሚያጠናክረው በሱማሌ ክልል የተደረገው ሰልፍ #አብዲ ኢሌን የሚያወግዝ እንጂ ሶዴፓን/ኢህአዴግ የሚጠየፍ አልነበረም፣ አብዲ ኢሌ በኦሮሚያ በጣም ስለሚጠላ ከ1ሚሊዬን ተፈናቃይ ዜጎች ጋር በተያያዘ የሱማሌ ወንድሞችን በማገዝ ኦሮሚያ ላይ ሰልፍ ይደረጋል የሚል ግምት ተይዞ የተወጠነ ይመስል ነበር። በታሰበለት መልኩ አልሄድ ስላላቸው ጠንሳሾቹ የሶማሌ ክልሉን ሰለፍ ገታ በማድረግ ወደ ኦሮሚያ ፊታቸውን አዞሩ ደህና ምክንያት ፈለጉ ከዛም ከወር በፊት ተፈርሞ ለኦሮሚያ ክልል መንግስት ያልደረሰ ደብዳቤ ሰካን ተደርጎ የተዘጋጀ ካርድ ነበር እሱን በመምዘዝ እንደገና ህዝቡን የለመደውን አደባባይ እንዲጎበኝ ማድረግ ተቻለ። አሁን ከባዱ ነገር በጉጂ የተደረገውን ተቃውሞ በመላ ኦሮሚያ ለማዳራስ ሌላ ከባድ አጀንዳ መፈጠር አለበት። በሴራ ኦሮሚያን የብጥብጥ ሜዳ በማድረግ ሙርሲ የደረሰበትን እነ አብይ ላይ ለመሞከር የሚፍጨረጨር ቡድን ያለ ይመስላል።
__ __

ከሚድሮክ ጋር የተያያዘውን ቅሬታ ለማ መገርሳ በአንድ ቀላጤ ወረቀት ድባቅ ይመታውና ተቃውሞውን ውኃ ይቸልስበታል ለምን ይህን ችግር ክልሉ እንደ ቀላል የሚያየው ጉዳይ አይሆንም። ደግሞም ከማንም በፊት ችግሩን በመዘገብ ለህዝብ እይታ ያቀረበው የክልሉ ሚዲያ #OBN ነው። በነገራችን ላይ ይሄ የሚድሮክ አወዛጋቢ ኢንቨስትመንት ጉዳይ ረጅም ዓመት የፈጀ ነው፣ ትዝ ይለኛል ዩንቨርሲቲ እያለን ሰልፍ በማድረጋችን ሚድሮክ ለአከባቢው ማህበረሰብ ልማት 30 ሚሊዮን ብር ረዳ የሚል ዜና በኢቲቪ ተላልፎ ነበር፣ ህዝብ ጋር የደረሰ አይመስለኝም። የፖለቲካውን ሴራ ሳቢና ልብ አንጠልጣይ የሚያደርገው ተቃውሞውን ወደ ሌሎች አከባቢዎች ለማስፋት የሚፈጠሩ ተጨማሪ አጀንዳዎች ናቸው።
__ __

ፖለቲካ በጣም ውስብስብ ነው። በምርጫ ሜዳ ያጣህውን በአደባባይ ነውጥ ለማስመለስ ትሯሯጣለህ፣ በድርድር ያስበላህውን እድል በሴራ ካርድ ለማስመለስ ታሴራለህ፣ 4ኪሎ ላይ የተበላህውን ቁማር ለማስመለስ #ሞያሌ ላይ ትጫወታለህ። ዶ/ር አብይ ኢትዮጵያን የሚዞረው ለምን ይመስልሀል? የመዞር ሱስ ስላለበት እንደማትለኝ ተስፋ አደርጋለው። በሱ ወደ ስልጣን መምጣት ብዙ ጥቅማቸውን የሚያጡ ቡድኖች አሉ፣ እነዚህ ቡድኖች ተራ ዜጋ እንዳይመስሉህ ትልቅ ሀብት የሚያዘዋወሩ፣ ከፍተኛ ኔትወርክ ከ ሸገር እስከ አወዳይ፣ ከመቀሌ እስከ አወዳይ፣ ከሸገር እስከ አሜሪካና አውሮፓ የተዘረጋ ሰንሰለታማ ትስስር ያላቸው ናቸው። ስለዚህ ይህን አደገኛ ቡድን ማሸነፍያ ዘዴ አንድና አንድ ብቻ ነው #የህዝብ የተባበረ ክንድ። ዶ/ሩ የሚንከራተተው ሴራውን የሚበጥስ የህዝብ ክንድ ለመፍጠር ነው።

የግብፁ #መሀመድ ሙርሱ ከቤተ-መንግስት ወኃኒ ቤት የገባበትን መንገድ እንኳን የደህንነት ተቋሙንና መከላከያውን በደምብ የሚያውቀው ዶ/ር አብይ ይቅርና ለእንደኔ አይነቱ ተራ ዜጋም ግልፅ ነው። እናም ሰውዬው እየሰራ ያለው ከታሰበለት ጉርጓድ በላይ ነው ለማለት ነው።

#ማጠቃለያ
***********
#ለማ መገርሳ እንዳሁኑ የሚተማመንበት ህዝብ ሳያፈራ፣ አምባገነኖች እግር ስር ቁጭ ብሎ “ህዝብ ካልፈለገው ወርቅ እንኳን ቢያፈስ ማስተር ፕላኑ እንጦሮጦስ ይጣላል” እንዳለ የሚረሳ ጉዳይ አይደለም። ስለዚህ ይህን የሚድሮክ ከባድ የጤና እክል እያስከተለ የኖረ ኢንቨስትመንት ጉዳይ ምንም የታዳጊ ወጣት ደም ሳንገብር እንደሚሰርዙት እርግጠኛ ነኝ።

Filed in: Amharic