>

ጊዜ ቦታ ያቀያየራቸው አባራሪና ተባራሪ (ጌታቸው ሽፈራው) 

(ከግራ ወደቀኝ አባራሪው ብ/ጀ ተክለ ብርሃን  እና አዲሱ የINSA ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህ)
የኢንፎርሜሽን መረብ ደሕንነት ኤጀንሲ (ኢመድኤ/INSA) አለቃ አዛዥ ናዛዥ የነበረው  ብ/ጄ  ተክለ ብርሃን ወ/አረጋይ በአንድ ወቅት ለትምህርት ወደ እንግሊዝ ሄዶ ነበር።
እሱ ለትምህርት በሄደበት ወቅት ዶ/ር አብይ ድርጅቱን ሲቪል ለማድረግ  ጥረት አድርጎ ነበር።  የፓርቲ አባል ያልሆኑ ተመራቂዎች እንዲቀጠሩ፣ ከመቀሌው ቴክኖሎጅ ተቋም ውጭ የተመረቀ ሰው ወደ ድርጅቱ እንዲገባ ሌላም ሌላም። ጀኔራሉ ሲመለስ አቧራ አስነሳ። አብይ ድርጅቱን የንግድ ድርጅት አደረገው ብሎ አብጠለጠለው። የተቃዋሚ መፈንጫ እንዳደረገው ሁሉ ነው ያሰበው። የሰራተኛው ፌስቡክ  ላይ አሰሳ ተጀመረ።
አብይ የጀመረውን ሁሉ ማፍረስ ጀመረ። የሻይ ማሽን ሳይቀር! ከዛ እነ አብይንም አውጥቶ ወረወራቸው። ከተወረወሩት ሰዎች መካከል አሁን አብይ የ INSA ዳይሬክተር ያደረገው ተመስገን ጥሩነህ አንዱ ነበር። ተመስገንን አብይ ወደ ድርጅቱ እንዳስገባቸው እቃዎች አውጥቶ ጥሎት የነበረው ብ/ጀ ተክለ ብርሃን፣ “በራሱ ፈቃድ” ለቅቋል።  ትህነግ/ሕወሓት ለሌላ ቦታ አጭታው ይሆናል እንጅ በቀላሉ ከስራ ውጭ የሚያደርጉት ሰው አይደለም። ይህ የአብይን እቃዎችና እነ አብይን፣ እነ ተመስገንን የወረወረ ሰው ዛሬ ከተመስገን ጋር እንዲህ ተጨባብጧል። በእርግጥ ተመስገን ዛሬም እንደ አዛዥ ሊያየው ይችላል!
Filed in: Amharic