>
5:13 pm - Tuesday April 19, 9960

አቶ መላኩ ፋንታ ለምን አይፈቱም? ስድስት አንኳር ምክንያቶች (ዘ ሚካኤል ጆርጅ)

ጽሁፉ በፍርድ ቤት በተጠረጠሩበት ክስ በአብዛኛው ነጻ የተባሉት አቶ መላኩ ፋንታ ለምን ከእስር ተፈተው ህክምናቸውን እንዲከታተሉ እንደማይደረግ ፍንጭ ይሰጣል በሚል እምነት የቀረበ ነው።
አንድ
የመጀመርያውን የ3 ዲ ካሜራ ያመጣው ቴዎድሮስ ተሾመ ነው። ሁለተኛውን ያመጣችው የበረከት ስምኦን ባለቤት ነች። ሆኖም አቶ መላኩ ያለ ሙያ እንዲህ አይነት መሳሪያ ማስገባት እንደማይፈቀድ ይነግራታል። መሳሪያው ይያዛል። በረከት አቶ መላኩ ጋር ይደውላል። አልሰማውም። ከዛም የ3 ሚሊዮን ብር ዘመናዊ ካሜራ ተወረሰ።
ሁለት
አቶ መላኩ ፈንታ ጎንደር በኢትዮጵያ ቀዳሚዋ የቱሪዝም ከተማ እንድትሆን
የጥምቀት ካርኒቫልን ያስጀምራል። የአጤ ቴዎድሮስ ሀውልት፣ የአጤ ቴዎድሮስ ቤተ መዘክር እንዲሰራ ሀሳብ ያቀርባል። ጎንደር ከተማ እና መተማ የወላለቁ ትምህርት ቤቶችን እንዲሰሩ ባለሀብቶች ያሰባስባል። በጎንደር ታዋቂ ሰው ሆነ። መለስ ዜናዊ ለመላኩ ፈንታ አንድ ይሁንታ ሰጥቶት ነበር።
መላኩ ጉምሩክ ሲቀጠር ለመለስ ጥያቄ አቀረበ “ሁለት አማራጭ አለኝ።
ወይ እንደተለመደው የራሴን ኑሮ የተሻለ ማድረግ ነው። ሁለተኛው ደግሞ የተሻለ ስራ መስራት ነው። ስሰራ ግን እንቅፋት አለ። ሙስና አለ። ጫና አለ። ይህን ጫና ለመቋቋም ከጎኔ ከሆኑ የተሻለ መስራት እችላለሁ። ከጎኔ ካልሆኑ እኔም ለራሴ ብቻ ነው የምጨነቀው።” ይለዋል። መለስ ከጎንህ እሆናለሁ የሚል ቃል ይሰጠዋል። በዚህ ምክንያት መለስ ጎንደርና አማራ ክልል ለመስራት በጀመረው፣ ካቢኔው ሁሉ መላኩን ይከተለዋል። በረከት
ችላ ተባለ። በተለይ ጎንደር በመወለዱ ለመደነቅ የሚጥረው፣ በጎንደር ጎዳናዎች አልፎ አልፎ እየታየ የሀገር ሰው ለመምሰል የሚጥረው በረከት ተረሳ። መላኩ አስረሳው።
በረከት ይህ የመላኩ ተቀባይነት እሱንና የህወሃት ወኪሎችን ዋጋ እንደሚያስከፍል ያውቃል። ህወሃትም ይህን ስጋት ይጋራዋል።
ሶስት
አማሮች ከደቡብ ሲባረሩ እነ በረከት የመጀመርያ የደገፉት የእነ መለስንና
የእነ ሽፈራውን ሀሳብ ነው። እንደ ተስፋፊ፣ እንደ ስደተኛ ነው የሚያዩዋቸው።
አንዳንድ ጥያቄዎች ሲቀርቡ፣ ተቃውሞ ሲበረታ ግን የደህዴን የአካባቢው
ካድሬዎች ጥፋት አድርገው አሳነሱት። መላኩ የታችኛው ካድሬ ብቻ
አይደለም። የላይውም አካል አለበት፣ ይጠና ብሎ ተከራከረ። ከእነ በረከት
ጋር ተመሳሳይ አቋም የነበረዉ ሽፈራው ሽጉጤ ድረስ መጠናት አለበት
የሚል ክርክር አቀረበ።ይህ እነ በረከትን አላስደሰተም፡፡ እነ መላኩ እነ
ሽፈራውም ተጠያቂ ናቸው ሲል ከእነ በረከት ጋር በዚህ ምክንያት አንድ
አንድ ተባብለዉ ተጋጭተዋል። “ጉሙሩክ አካባቢ ያሉ ችግሮች እንዴት
ታያቸዋለህ?” የሚል ጥያቄ በረከት ለመላኩ ያቀርባል፡፡ “ስራችን እየሰራን
ነዉ ግን አንዳንድ ሰዎች ያስቸግሩናል፡፡ እነሱን ብትሰበስቡልን ጥሩ ነዉ፡፡
እንዲያዉም ያንተ ኔትወርኮች ናቸዉ ያስቸገሩን” ይላል መላኩ፡፡ በዚህ
በረከት እጅግ በመናደዱ ከህወሃት ሰወች ጋር ሌት ተቀን ያሴር ነበር፡፡
አራት
በረከት ስምኦን የቀድሞው የጉምሩክ አቃቤ ሕግ የነበረውን ሳሙኤል ታደሰን
ከተማ ከበደ 3 ሚሊዮን ብር እንዲሰጠው ይልክበታል። አቶ ከተማ ደረቅ
ሰው ነው። አልሰጥም ይላል። በ2002 አቶ መላኩ የአማራ ባለሀብቶች
አልማን እንዲረዱ እያስተባበረ ነው። የእነዚህ ባለሀብቶች ትብብር
ለህወሓትም አደጋ ነበር። እነ በረከትም ይህ ትብብር በመላኩ በኩል መሆኑ
ባለሀብቱንም ካድሬውንም ነጠቀን ብለው ፈርተዋል። እንደ አዲስ ንቅናቄም
ነው ያዩት። በዚህ መድረክ ከተማ ከበደ ነበር። መላኩ አስተባባሪ ነው
፤ለአልማ መዋጮ። መላኩና ከተማ አይተዋወቁም። አሁን የተከሰሱበት በዛ
መድረክ ተገናኝተው ከተማ ለመላኩ ጉቦ ሰጥቶታል የሚል ነው። አቶ ከተማ
በመላኩ ላይ መስክርበት ተብሎ አልመሰክርም ብሎ ነው የታሰረው።
ለበረከት በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ነው የሆነለት፡፡
አምስት
የመከላከያ ጀኔራሎች በአንድ ወቅት አንድ መብት ተፈቅዶላቸው ነበር።
መሬት ተሰጥቷቸዋል። የቤት መስርያ ነው። የቤት መስርያ ቁሳቁሱን ደግሞ ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ ተፈቅዶላቸዋል። ሆኖም እነ ሳሞራ ከቤት መስርያው ውጭ የሚሸጥ ቁሳቁስን ከቀረጥ ነፃ አስገቡልኝ ማለት ጀመሩ። መላኩ አይሆንም አለ። መለስ ሽፋን እሰጥሃለሁ ባለው መሰረት መላኩ ለመለስ ጀኔራሎቹ እያስቸገሩት እንደሆነ ገለፀለት። መለስ ጀኔራሎቹን ፣
ዋናው ሳሞራ ነው፣ አዜብንም ጨምሮ አርፋችሁ ተቀመጡ አላቸው። እነ ሳሞራ ጥቅማቸው ቀረባቸው። መላኩ ስላስወቀሳቸው የተናቁ ክብራቸው የተነካ አድርገው አዩት። ይህ ጥቅም የእነ ጌታቸው አሰፋም ጭምር ነው።
ጌታቸው አሰፋም አኮረፈ።።ለመለስ ከጌታቸው አሰፋ ይልቅ ታማኝ የነበረው ከእነ መላኩ ጋር የታሰረው የጌታቸው ምክትል ገ/ስላሴ ነበር። መለስ ሲሞት
የመለስ ድጋፍ የነበረው መላኩ እና የመለስ ተመራጭ የነበረውን ምክትሉን
አሳስሯል፡፡
ስድስት
ከዚህ ባሻገር አቶ መላኩ በአማራ ክልል ኢንቨስትመንት ለመሳብ፣ ቱሪዝም
ለመሳብ፣ አልማን ለማጠናከር ያደርገው የነበረው ጥረት በሙሉ የትግራይን
ኢኮኖሚ የሚገዳደር አድርገው አይተውታል። ጀኔራሎቹ ና እነ ጌታቸው በነፃ እንዳያስገቡ መለስን ሽፋን አድርጎ ሲያሳጣቸው ቆይቷል።
እነ መላኩ 60 አካባቢ ነበሩ የተከሰሱት። አሁን አንድ ኦሮሞ፣ 6 አማራ፣ አንድ ትግሬ (ገብረወሃድ) ቀርተዋል። አብዛኛዎቹ የትግራይ ባለሀብቶች በቅርቡ ተፈትተዋል። በዋስ። አቶ ከተማ ከበደ ዋስትና የተከለከለበት ክስ እነሱ ዋስትና ከተፈቀደላቸው ያነሰ ነበር። የደህንነት ሚኒስትሩ ወልደስላሴ ወራቶች ብቻ ይቀሩታል።።ተፈርዶበታል። በቅርቡ ይወጣል። የእነዚህ ሰዎች ጥፋት ምንድነው? ብሄራቸው አይደለምን?
Filed in: Amharic