>
5:13 pm - Thursday April 19, 3477

" ምትሃተኛው ደራሲ የይድረሱልኝ ጥሪውን አቅርቧል !" (ብሩክ ተፈራ)

በ 31  ዓመቱ  13  መፅሃፍትን  ፅፏል  ። ( ተከርቸም ፣ ተልሚድ ፣ የወንድ ምጥ ፣ ዴርቶጋዳ ፣ የቀንድ አውጣ ኑሮ ፣ ራማቶሃራ ፣ ዣንቶዣራ ፣ ክቡር ድንጋይ ፣ዮራቶራድ ፣ ሜሎስ ፣ የኦጋዴን ድመቶች  )   የረሳኋቸውን  ሁለቱን  አስታውሱኝ  እስኪ 🙂 ።
 በተለይም  ዴርቶጋዳ  በተሰኘው  መፅሃፉ  250,000  ኮፒ  በመሸጥ  በሃገራችን   ከፍተኛ  የሽያጭ  ሪከርዱን  ሰብሯል ።  ይህ ዴርቶጋዳ  የተሰኘው  መፅሃፍ  በሃገራች  ለይ  ከመፅሃፍ  ቅዱስ /ቁርዐን  በመቀጠል  በሁሉም  ቤት  ውስጥ  የሚገኝ  ተነባቢ  መፅሃፍ  ነው ።  ስለዚህ  መፅሃፉ  በአንድ  ወቅት  ለአንድ  የበቁ  አባት  አጫውቻቸው   እውነትነቱን  ስጠይቅ  ፤ መፅሃፉን  አምጣልኝ  አሉኝ  ፤  ወስጄም  ሰጠኋቸው  ታድያ  አንብበውት  ሲመልሱልኝ  ”  ይህ መፅሃፍ  80 ፐርሰንቱ  እውነት  ነው ! ”  ያሉኝን  አልረሳውም ።  ይስመዓከ  ወርቁ   ጣና  በደጋ  እሲፋኖስ  ገዳም  ተወልዶ  ማደጉንና  በጀርባውም  ለይ  የ ” ቶ ”  ፊደል  ቅርፅ  ያለው  ንቅሳት  እንዳለበት  ሚናገሩ  አሉ ።
ይስመዐከ  የራሱን  ህትመት  ቤት  በመክፈት  በሀገራችን ለይ እያንሰራራ  ያለውን ጣራ  የነካ   የመፅሀፍ  ሽያጭ  ለማረጋጋት  እና  ትውልዱን  ወደንባብ  ለማምጣት  የበኩሉን  አስተዋዕፆ  አድሮጓል ።   ነገር  ግን  ” ማንም  የቆመ  ቢመስለው  እንዳይወድቅ  ይጠንቀቅ!  ” ይላልና  መፅሃፉ ፤  ዛሬ  ለይ  በታላቁ  ደራሲ  ይስመዓከ  ወርቁ  ህይወት  ለይ  የታሰበው   ሳይሆን  ያልታሰበው  ሆኗል ።  ከሀዋሳ  ወደሻሸመኔ  በሚወስደው  መንገድ  ለይ  በወርሃ  መስከረም  ቪትትዝ  መኪናውን  እየነዳ  በነበረበት  ወቅት  ኩርባውን  ሊዞር  ሲል  ፤ ኤፍኤስታር  የተባለ ከባድ  ተሽከርካሪ  ባልታሰበ  ሁኔታ  እላዩ  ለይ  በመውጣት  ግጭት  አድርሶበት   ቀላል  የማይባል  አደጋ  ገጥሞታል ።
በአደጋው  ጭንቅላቱ  አካባቢ  ከፍተኛ  ጉዳት  የደረሰበት  ይስማዕከ  ከስምንት  ወራት  ህክምና  በኋላ  ዛሬም  ከህመሙ  አገግሞ  ከአልጋ  ለይ  ቢነሳም ጭንቅላቱ ላይ ከደረሰበት አሰቃቄ የራስ ቅል የመሰበር አደጋ የተነሳ አንደበቱን አፍታትቶ ቃላት ማውጣት እና ሀሳቡን መግለጽ አልቻለም ።   ይስማዕከ  በጤናው  ላይ  ከቀን  ወደ  ቀን  ለውጥ  ባለማሳየቱ  እና  ጭራሽ  ህመሙ   እየተደራረበበት  በመሄዱ  ሳቢያ  የኛ  ሀገር  ዶክተሮች  ተስፋ  ቆርጠዋል ።  ውጪ  ሄዶ  ለመታከም  ደሞ  አቅም  አንሶታል ።  ስለዚህ  ህዝብ   ፊት  ቆሞ እርዳታ  መጠየቅ  ባይፈልግም  አማራጭ  አጥቷልና  በአደባባይ  ወጥቶ  የኢትዮጵያን  ህዝብ  ድረሱልኝ  ብሏል ።  ምትሃተኛው  ደራሲ  የይድረሱልኝ  ጥሪውን  አቅርቧል ።  ይስማዕከ  ደራሲ  ብቻ  ሳይሆን  ቅርሳችንም  ጭምር  ነው  ።  በቅርቡ  ጦምሬው  እንደነበረው  Marvel Studio   “The Black Panter ” ን  ሲሰራ  የአድዋን  ታሪክ  ብቻ  ሳይሆን  የዴርቶጋዳን  ሃሳብንም  ዘርፋል ።   ይህን  ደራሲ  ለዛ  ነው  ቅርሳችን  ነው  የምለው ።  ፈጣሪ  ፈውሶት  በእነዛ  ብዕሮቹ  መልሰን  እንድናገኘው  ምኞቴ  ነው ።
መርዳት  ለምትፈልጉ
በባንክ  ቁጥር  1000243275408  ወይም  በስልክ  ቁጥር  0904388666  መደወል  ትችላላችሁ ።
Filed in: Amharic