>
5:13 pm - Thursday April 19, 9906

የህወሃት ሰዎች አፈነግጠው ፋብሪካ ሲገነቡ፣ ሲነግዱ አማራ ወይም ኦሮሞ እጣው ስደት አልያም እስር አይደለምን? (ሚኪ አምሀራ)

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ እኔ የምልወት ነገር ቢኖር 1740 አማራ የሞተበት፤በሽወች የተፈናቀሉት፤ በሽወች የተሰደዱት የዉሃ እና የልማት ጉዳይ አይደለም፡፡ ይሄን ለማወቅ የሚስትወትን ወላጆች አርማጭሆ ናቸዉ ተብሏል ማታ ይጠይቋት ስለ ወልቃይት ጉዳይ ፈትፍታ ትነግረዎታለች፡፡ ሌላዉ የተሳሳቱት ወልቃይት ዲያስፖራ ስላራገበዉ ነዉ ያሉት ነዉ፡፡ ዲስፖራ እንዲያዉም የወልቃይት ጉዳይ የጎጥ ነዉ ብሎን አልቀበል ብሎን መሬት ላይ ባሉ አማራወች በተደራጀ መልኩ የተሰራበት ነዉ፡፡ ጎንደር እኮ እብሪተኛ የህወሃት ወታደር መቶ ህጻን ልጆች ባሉበት ቤት፤ እርጉዝ ሴትዮ ባለችበት ቤት ስለ ወልቃይት ቀስቅሰሃል ተብሎ ቦንብ ቤቱ ላይ ሲዘንብበት ያደረ ነዉ፡፡
ሌላዉ የሳቱት ነገር በወልቃይት ጉዳይ የአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን 1.5 ሚሊየን የብአዴን አባላት ጥያቄ መሆኑን አለማወቅዎ ነዉ፡፡ የእነ አቶ ገዱ ጥያቄ ነዉ፡፡ ሌላዉ ቀርቶ እንኳን በሚዲያ ባይናገረዉም በዉስጥ ስብሰባወች አቶ በረከት ሳይቀር የወልቃይት ጥያቄ ተገቢ መሆኑን ያምናል፡፡ አንድም የብአዴን ሰዉ እርስወ እንዳሉት የወልቃይት ጉዳይ የዉሃ ጉዳይ ነዉ አላሉም ባይሆን ጥያቄዉ መጀመሪያ ባለበት ክልል ይቅረብ ማለታቸዉ ነዉ ከእኛ ጋር የሚያለያየን፡፡ አዲስ አባባ እኮ ከ6 እስከ 10 የሚደርሱ የህወሃት ዳኞች ተመድበዉ አንድ እራሱን የቻለ ፍርድ ቤት እኮ አለ የወልቃይትን ተከሳሾች ብቻ የሚያይ (ልደታ 4ተኛ እና 19ኛ ምድብ ችሎ)፡፡ እንዳልኮዎት በሽወች የሚቆጠሩ የወልቃይት አማራ እኮ  ማእከላዊና ቂሊንጦ እስር ቤቶች ነዉ ያለዉ፡፡ ይሄን ህገመንግስታዊ ጥያቄ በአግባቡ እንዲፈታ አቅጣጫ ይሰጣሉ እንጅ የልማት ጉዳይ ነዉ ተብሎ የሚታለፍ አይደለም፡፡ የትግራይና የአማራን ህዝብ እስከዉዲያኛዉ እየነጠለዉ ያለዉ ጉዳይ የዉሃ እጥረት አይደለም፡፡ የማንነትና የመሬት ጥያቄ ነዉ፡፡ ለአንድ ሚሊየን ኦሮሞና ለሽወች ሶማሌወች መፈናቀልና ሞት እኮ የመጣዉ የዉሃ ወይም የልማት ጉዳይ አይደልም፡፡ በ4 እና በ 5 ቀበሌወች መስማማት አቅቷችሁ ነዉ፡፡ የኦሮሞ ልጆች ለፍትህ እና ለእኩልነት ነዉ የተዋደቁት ካልን የአማራ ልጆች ዉሃ ስልጠማቸዉ ነዉ የምንልበት አጋጣሚ የለም ከሆነም hypocrisy ነዉ፡፡ ይሄ ትልቅ ክህደት ነዉ፡፡ ክህደት ደግሞ የኦሮሞ ህዝብ መገለጫም ባህሪም አይደለም፡፡ ባለፈዉ በአማራ ስም ደመቀ መኮነን እንደካዳችሁ ስንሰማ የአማራ ህዝብ ከዳር እስከዳር አማራን እንደማይወክል፤ የአማራ መገለጫ እንዳልሆነ ሆ ብለን አዉግዘነዉ ነዉ የእርስወ ምርጫ ላይ ያችን ክደት ለመሻር ያመቻቸለወት፡፡ እርስወም ይሄን ክህደት እንደገና ሊዉጧት ግድ ይላል፡፡
የአርማጭሆ እና የወልቃይት ዲያሰፓራወች ወደ አገር ቤት ኑ
ይሄ እንዴት አይነት ቀልድ ነዉ፡፡ እርስወ የደህንነት ቢሮዉን ሲመሩ በነበሩበት ግዜ እኮ ኤርፖርት ላይ ፎቷቸዉና ስም ዝርዝራቸዉ ተመዝግቦ የደህንነት ክትትል የሚደረግባቸዉ ሰወች ቁጥር ከ 200 መቶ አይበልጡም ነበር፡፡ አሁን እኮ የ8ሺህ ዲያስፖራ 3ሺህ ኦሮሞ 5ሺህ አማራ በቤተ መዛግብት የሚያክል ዶሴ ሰም ዝርዝራቸዉ እስከ ዲቴል መረጃቸዉ ተመዝግቦ ነዉ ያለዉ፡፡ ፎቷቸዉ ከነስማቸዉ ዳታ ቤዝ ዉስጥ ነዉ ያለ፡፡ ያች ኤርፖርት ላይ ያለችዉ የ4 በ4 የመመርመሪያ ክፍል ዉስጥ የተቀመጠ የ8ሺህ ኦሮሞ እና አማራ ዲያስፖራ ዝርዝር የያዘ ባህር መዝገብ ወቶ ባደባባይ ሳታቃጥሉት ማነዉ እንዴ ሚመጣዉ ለዛዉም የወልቃይት አማራ፡፡ ለመሞት ነዉ፡፡ሌላዉ ቀርቶ በዛ ኤርፖርት እኮ ያፈነገጡ የብአዴንና የኦህዴድ ሰወች እንዳይወጡና እንዳይገቡ የሚደረግበት የገነት በር ያህል የጠበበ እኮ ነዉ፡፡ የብአዴኑ ጄኔራል አበባዉ በተራ የህወሃት ደህንነት በጥፊ ተብሎ ፓስፖርት ተቀምቶ ያለስራ ስንት አመት ሆነዉ ከተቀመጠ፡፡ አምና የብአዴን ማእከላዊ ስብሰባ ላይ ተናገረ ተብሎ የሲቪል ሰርቪስ ሃላፊዉ ሻምበል ከበደ አስረስ ቻይና ለስራ ሊሄድ ሲል ተይዞ 2 ቀን አልታሰረም እንዴ፡፡ ከስራዉስ አልተባረረም እንዴ፡፡ ገዱ ሚስቱን አሜሪካ ለማሳከም ሊወጣ ሲል ኤርፖርት ላይ ደህንነት አላንገራገረዉም እንዴ ሲመለስ ከግንቦት ሰባት ሰወች ጋር ተገናኝኝተሃል ተብሎ ሃራስ አልተደረግም እንዴ፡፡ አንድ ካሊፎርኒያ ለረዠም ጊዜ የኖረ ኦሮሞ ቤተሰብ ሊጠይቅ እንደመጣ ስሙ እዛ መዝገብ ላይ ተገኝቶ ተይዞ እስር ቤት እየደለም እንዴ ያለዉ፡፡ ከእንግሊዝ ቤተሰቡን ሊጠይቅ የመጣ አማራ ማእከላዊ እየደለም እንዴ ያለዉ፡፡ስንት የኦሮሞ ልጆች ስማቸዉ በደህንነት ክትትል ስለሚደረግባቸዉ ከየመንና ኬንያ ወደ አገር ቤት ለመግባት አልችል ብለዉ እየሞቱ እይደለም እንዴ ያሉት፡፡ ስንት ሺህ አማራ በሊቢያ የባህር አዉሬ ይብላኝ ብሎ በእግሩ የሚጓዘዉ በህጋዊ መንገድ እንዳይወጣ ታግዶ እይደለም እንዴ፡፡ ህወሃትን ለማፍረስ የተንቀሳቀሱት እነ ስየ እና ገብሩ እንደፈለጉ አገራቸዉ ሲገቡ ሲወጡ ገና ሚዲያ ላይ ተናግረዋል የተባሉ በነሱ ደረጃ ያሉ የአማራና የኦሮሞ ፖለቲከኞ ለምሳሌ እነ ታማኝ እንደዛ ያደርጋሉ እንዴ፡፡ የኦነጉ ሌንጮ አገሬ ብሎ ኤርፖርት ድረስ መቶ ወዲያዉ በ 3 ሰአት ዉስጥ አልመለሳችሁትም እንዴ አትገባም ብላቸሁ፡፡ የህወሃት ሰወች ሲያፈነግጡ ፍብሪካ ተሰቷቸዉ የዉጭ ንግድ ሲነግዱ አማራ ወይም ኦሮሞ ከሆነ በርሃ ለበርሃ ተንከራቶ እይደም ወይ የሚዎጣዉ፡፡እነ ጁነዲን ሳዶ እኮ የራስወ ፓርቲ አባል ናቸዉ ይሄን እጣ ፋንታ የቀመሱ፡፡ ሰሞኑን ደብዳቤ አልደረሰወትም እንዴ ለፒ.ኤች.ዲ ምርምር የመጡ ሁለት አማራ እና አንድ የኦሮሞ ተማሪዎች እንዳይወጡ ታግደዉ ትምህርታቸዉ ተስተጓሎባቸዉ የል እንዴ፡፡ ከሲያትል ቤተሰብ ልትጠይቅ የመጣች የአርማጭሆ/ጎንደር ልጅ ሰልፍ ላይ ታይተሻል ተብላ ከኤርፖርት አንዳትወጣ ታግዳ ከሁለት ወር በኋላ በዘመድ በረከት ተጠይቆ እየደለም እንዴ የወጣችዉ፡፡ንገሩኝ ባይ፡፡ እና እንዴት ነዉ ዝም ብሎ አንድም እርምጃ ሳወስዱ የአርማጭሆና የወልቃይት ዲያስፖራወች ኑ እና እዩ የሚባለዉ፡፡ መጀመሪያ አገሪቱን ለሁሉም ዜጎች እኩል የምትሰራ ትሁን፡፡ አሁንም ህወሃት ነዉ ወደ ስልጣን ያመጣኝ አይነት የቅዠት ጉዞ አያስፈልግም፡፡ በህዝብ ግፊት ነዉ የመጡት፡፡ በእርግጥ ስለ ወልቃይትም ሆነ ስለ ሌላ ነገር ከህወሃት መስመር በወጣ ቢናገሩ የግብጹ በህዝብ ግፊት የመጣዉ በኋላም በወታደሩ መፈንቅለ መንግስት የተደረገበት የሙርሲ እጣ ፈንታ እንዳይደርስወ ስለሰጉ ይሆናል፡፡
ሶሻል ሚዲያ
በነገራችን ላይ እርስዎ በሶሻል ሚዲያና በዲያስፖራ የተመረጡ መሪ ነዋት፡፡የሶሻል ሚዲያ ዉጤት እንጅ ኢህአዴግ ወዶ እና ፈልጎ ያመጣወት አይደለም፡፡ ዝም ብለዉ ሙገሳዉን ለህወሃት አይስጡት፡፡ ስለዚህም ዲያስፖራን እና ሶሻል ሚዲያን ሊያጣጥሉ አይችሉም፡፡ እነ ጃዋርና ሌሎች የዲያስፖራ አክቲቪስቶች ናቸዉ ሶሻል ሚዲያን በመጠቀም ህወሃት ላይ ጫና በመፍጠር ህብረተሰቡን በማስተማር እርስወ ወደ ሰልጣን መንበሩ እንዲመጡ ያደረገወት፡፡ ሶሻል ሚዲያ ባይኖር እማ ይኄኔ የእርስወ እጣ ፈንታም እንደወንድሞቻችን በኬንያ በኩል መዉጣት ነበር፡፡ ሌላዉ ለትግራይ ህዝብ ክብር ሲባል እስረኞችን ለቀናል አሁን ያሉት ከ 5 ወይም ከ 10 አይበልጡም ብለዋል፡፡ የታሰረ የህወሃት ኮንትሮባንዲስት እየዞሩ ሲያስፈቱ ከ97ሺህ ባለይ የአማራ እስረኛ ከ88  ሺህ በላይ የኦሮሞ እስረኛ (ከብርሃነ መስቀል የወሰድኩት ነዉ) ያሉበትን ጉዳይ አይተዋል ወይ፡፡ ሲጀምርስ እንዴት አንድ ጠቅላይ ሚኒስቴር እስር ቤት ወርዶ ብሄር ቆጥሮ የእስረኛ ቁጥር ያረጋግጣል፡፡ አገሪቱ የሁሉም ሁና ለመቀጠሏ ምንም ማስተማመኛ የለም፡፡
ለአማራ አክቲቪስቶች
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እኛ ጋ ሳይመጣ ሌላ ቦታ ሄደ፤ በትግርኛ ወይም በሌላ ቋንቋ አወራ፤ ትግራይን የኢትዮጵያ እትብት ነች አለ የሚል የአማራን ህዝብ ጥያቄ የማይመጥንና የማይመለከት ብሎም ትልልቁን የአማራን ህዝብ ጥያቄ የሚሸፍን የህወሃት አክቲቪስቶች የሚሰጡንን አጀንዳ ይዞ ማራገብ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ለምን በዙሉኛ አያወራም፤ ለምንስ ትግራይ የአለም አምብርት ናት አይልም፡፡ ይሄ ከምናካሂደዉ ትልልቅና አንገብጋቢ አጀንዳችን ጋር እንዴት ነዉ የሚሄደዉ፡፡ በእንደዚህ አይነት ትንንሽ ነገሮች ለምን አንገብጋቢ ጉዳዮቻችን እንሸፍፍናቸዋለን፡፡ የመሬት፤ የማንነት፤ የኢኮኖሚና የፖለቲካ እኩልነት፤ ከ 100 ሺህ በላይ እስረኛ አማሮች ፍትህ፤ ከ1700 በላይ በአጋዚ ለተገደሉ እንንዲሁም የአካል ጉዳተኛ ለሆኑ አስቸኳይ ፍትህ ነዉ እየጠየቅን ያለዉ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስቴሩ ንግግር፤የተጠቀመዉ ቋንቋ፤ የሄደበት አካባቢ ለአማራ ህዝብ የሚፈይድለት አንዳች ነገር የለም፡፡ ከፈለገ የወፍ ቋንቋ ይጠቀም፡፡ ለነገሩ የአማራ አክቲቪስት የወልቃይትን ጉዳይ ነዉ እያወራን ያለነዉ ይሄን በትግርኛ አወራ ምናምን የሚሉን አነሱዉ እራሳቸዉ ናቸዉ፡፡ እንደዛ እያወራ ያለ አማራ ካለ መስተካከል አለበት፡፡ we should not lose the big picture. አሁንም ሰዉየዉ እጅግ የመረጃ ክፍተት አንዳለበት ያሳዉቃል፡፡ ስለዚህም ጥያቄወቻችን በፈርጅ በፈርጁና በተጠናከረ መልኩ ልናስተጋባ ይገባል፡፡ ጥያቄወቻችን ለሰዉየዉ ባግባቡ እንዲደርሰዉ በተቻለ መጠን ሎጂካል ሆነን እየተመካከርን በሚሄድበት ቦታ ሁሉ ጥያቄወቹ እንዲነሱ ለህዝባችን ማስተማር አለብን፡፡ ለሱ ብቻ ሳይሆን ለህወሃትም ለብአዴንም መድረስ ያለባቸዉን ጥያቄወች ነዉ አዉጥተን መወያየትና ማሰራጨት ያለብን፡፡ ባንድም በሌላ መልኩ ይደርሳቸዋል፡፡ መበሳጨትና መነጫነጭ አያስፈልግም፡፡ የወልቃይትን ጉዳይ አብይም ይሁን ህወሃት ወይም ብአዴን በቀላሉ የሚፈቱት ጉዳይ አይደለም፡፡ የሚፈታዉ እኛ በኢኮኖሚ ስንጠነክር፤ የተማረና ጠያቂ ማህበረሰብ ስንፈጥርና እንዲሁም ቀጥታ ከትግራይ ህዝብ ጋር በመነጋገር ነዉ የምንፈታዉ፡፡ የትግራይ ህዝብ ወልቃይት የማን አንደሆነ ጠንቅቆ ያዉቃል፡፡ አላዉቅም ካለ አከሱም ጺወን ወስደን እናስምላቸዋለን፡፡
Filed in: Amharic