>

የኢንሳ እና የሜቴክ ዋና ዳይሬክተሮች የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ 

ወዲ ሻምበል
 (ሜ/ጀነራል ተክለብርሀን ወልደአረጋይ እና ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው) የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ ። የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ተክለብርሀን ወልደአረጋይ እና የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ባለፈው ሰኞ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የስራ መልቂያ ደብዳቤ ማቅረባቸውን ታማኝ ምንጮች ለአውራምባ ታይምስ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለቱም ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ጥያቄ እስካሁን አልተቀበሉትም። ኃላፊዎቹ የመልቀቂያ ደብዳቤ ለማቅረብ ያስገደዳቸው ምክንያት ምን እንደሆነ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። የሁለቱም ተቋማት ኃላፊዎች ተጠሪነታቸው ለአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር እንደሆነ ይታወቃል።
Major General Teklebrhan Wolearegay of INSA and MeTEC chief Major General Kinfe Dagnew , have reportedly submited letter of resignation to Prime minister Abiy Ahmed, last monday, sources disclosed to Awramba times.
Prime Minister Abiy didn’t yet approve the resignation request of both senior military officers. Directors of both agencies are accountable to the nation’s Prime minister.
                    ,,,,
የሜቴክ ኃላፊ ብ/ጄ/ ክንፈ ዳኘው  “ማነው የላከህ ፣ በረከት ነው? ሀይለማርያም ራሱ ይምጣ!” ነበር መልሳቸው
ፍቅሬ ስንታየሁ እንደጻፈው
1) 10 የስኳር ፋብሪካ
2) 2 የማዳበሪያ ፋብሪካ
3) ሳምንት ሳይሰሩ የተበላሹ የአዲስ አበባ ባቡሮች
4)ሰባት አመት ኦዲት ያልተደረገ የአባይ ግድብ
5)700 የተበላሹና ያልተረከቡ የአዲስ አበባ አውቶብሶች
6)በሺህ የሚቆጠሩ በየከተማው የፈነዱ ትራንስፎርመሮች
7)በሚሊዮን የሚቆጠሩ የመንግስት ተሽከርካሪዎችና ለገበሬወች የተሸጡ ትራክተሮች
8 )በሜቴክ የተሰበሰበ የቀድሞው የጅቡቲ አዲሳባ ባቡር ሀዲ፣ ብዙ የቀድሞና ያሁኑ የመከላከያ ፋብሪካወች
9)ሌሎች ብዙ በህዝብ ግብርና በከፍተኛ ወለድ ከውጭ ሀገር በብድር የተጀመሩ ፕሮጀክቶች
በግምት 200 ቢሊዮን ብር የሚደርሱ የመንግስት ፕሮጀክቶችን የት እንደደረሱ ሳይጠየቁ፣ ሳያብራሩ፣ ኦዲት ሳይደረጉ፣ ሲያስለቅሱት የኖሩትን ፓርላማ እንኳን አንድ ቀን ቀርበው ማብራሪያ ሳይሰጡ መልቀቂያ አስገብተዋል።
  በተጨማሪም!
1/ ሰውየው ሜቴክን ባስተዳደሩበት አስር አመት አንድም ጊዜ ለሚዲያ ቀርበው አያውቁም። ከአማረ አረጋዊ ሪፖርተር ውጭ ስለሳቸው ሆነ ድርጅታቸው የሚናገር የለም።
2/ድርጅታቸው በፓርላማ ቀርበው ማብራሪያ ሰጥተው አያውቁም። ተራ ባለሙያ ልከው ግልፅ ያልሆነ መልስ ይሰጣሉ።
3/በሀገሪቱ እሳቸውን የሚናገር ወይም የሚያዝ አንድም ሰው የለም፣ ጠ/ሚኒስተሩን ጨምሮ
4/ለምልከታ የሄዱ ባለሙያወች “ማነው የላከህ ፣ በረከት ነው? ሀይለማርያም። ራሱ ይምጣ!” እያሉ ከበር ሳያስገቡ እንዲመለሱ ያዛሉ ይባላል።
Filed in: Amharic