>

"ሰኞ ተረገዝኩ ፣ ማክሰኞ ተወለድኩ ፣ እሮብ ንግግር አድርጌ አርብ ሞትኩኝ" (ሼሮኒካ መላኩ) 

አሁንም አቢይ አህመድ  የተሰራበትን ” Made in ” እየፈለኩ ነው። ፎርጅድ እና ሳልባጅ  ይሆን ወይስ ኦሪጅናል የሚለውን በቅርብ እንደርስበታለን። ነፍሱን ይማረውና  ሀይለማሪያም ጀርባው ላይ ያስነቀሰው ታቱ ” Made in Tigray “ይል ነበር።
 ግንባሩ ላይ ታርጋ ባይኖርም ማንነቱን በብላሽ ሸጦ  ፈረንጆቹ More catholic than the pop እንደሚሉት ሆኖ አረፈው። አሁን የሀይለማሪያም የስልጣን ዘመን ምንም ያልተፃፈበት የታሪክ ሌጣ ገፅ ሆኖ አለፈ።
የአቢይ የመቀሌ ጉዞ   ባወጣው ባወርደው ትርጉሙ አልገባኝም ። 
 አቢይ አህመድ መቀሌ በመሄድ የሚያናግራቸው በአንድ ወቅት ኮል መንግስቱ ሃይለማርያም “የኢትዮያ ህዝብ ሆይ እነዚህን የእናት ጡት ነካሽ ነቀዞች ተባብረን፡እናጥፋቸው። አለበለዚያ ያጠፉናል! ” እያለ ሲዋጋቸው  የተሰናከሉ “የናት ጡት ነካሽ ” የጦር ጉዳተኞችን ነው ተብሏል።
 እነሱን የሚያናግረው ለሎሌነት የማረጋገጫ መሀተም ለማስመታት እና ጫማ ለመላስ ከሆነ “ሰኞ ተረገዝኩ ፣ ማክሰኞ ተወለድኩ ፣ እሮብ ንግግር አድርጌ አርብ ሞትኩኝ ።”  ይሆናል ታሪኩ  ።
አቢይ አህመድ ከቅርብ ጊዜ ታሪክ ጥሩ ትምህርት መማር ያለበት መሆኑን እኔ ማስገንዘብ ያለብኝ አይመስለኝም። ሀይለማሪያም ደሳለኝ  የመሪነት ግርማና ሞገሱ ተገፎ መጫወቻ የሆነው ትግሬ አገር ሄዶ …” የኢትዮጵያ ህዝብ ውለታችሁን በመቶ አመት ከፍሎ አይጨርሰውም ” የሚል አሳፋሪ ንግግር ካደረገ በኋላ ነው።
አዎ ልክነበር  የሶማሌ  ክልልን  መጎብኘቱ  ምክንያቱም  ከፍተኛ  ቀውስ የተከሰተበትና  ሊከሰት የሚችልበት  በመሆኑ ፡፡
አዎ  ልክነው  የአምቦ  ጉብኝቱ  ምክንያቱም  የአንቦ  ህዝብ  ትግል  የጀመረው  ገና  ጥዋት  በ19 81 ዓ.ም ወያኔ  ሊገባሲል  ባለው ሀይል  እንዳይገባ ተጋድሎ በመመለስ  እናም  ለ27 ዓመት የበቀል  መወጫ ሆኖ በመኖሩና  ለአመፅም ሲነሳ ያለውን ሳያደርግ  የማይተኛ  ህዝብ በመሆኑ፡፡ እዚህ ጋ  ሌሎች  ክልሎች አልታገሉም  እያልኩ አይደለም፡፡
እንግዲህ  ቀጥሎ  የትግሉ  ሞተርና  በርካቶች  ህይወታቸውን  ያጡበት በርካቶች ለእስርና  እንግልት  የተዳረጉበት  ፡ያልተፈታ  የማንነት  ጥያቄ ያለበት ፣በብዙ አቅጣጫ  የመሬት ጥያቄ ያለበት ፣አልፎ  ተርፎ   ከጎረቤት  ሀገር  ከሱዳን    ጋር  በተደጋጋሚ  ጦር  ሰብቆ  የሱዳንን ወታደር የሚታገል  ገበሬ  ያለበት  አማራው  ክልል  እያለ  ፡ይበደልም  ይድላው  ምንም  ድምፅ  ተሠምቶበት  የማያውቀውን የትግራይ ህዝብ መቀሌ  ድረስ ሄዶ ማነጋገራቸው ግራ የሚያጋባ ከመሆኑም በላይ   “የትግራይ ሕዝብ የኢትዮጵያ ፈጣሪ ነው …. የትግራይ ሕዝብ ለኢትዮጵያ ፈጣሪዋ ብቻ ሳይሆን ሞተርም ነው!”   የሚለው ንግግራቸው በዘረኝነት ክፉ ደዌ ተጠቅቶ ዘመኑን ሁሉ በኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ ላይ አቂሞ ብዙ ሴራዎችን ሲያውጠነጥን ከኖረው ከአቶ መለስ “…. ወርቂ ህዝቢ ትግራይ…. እንኳንም ከእናንተ ተወለድኩ” ከአንድ መንግስት የማይጠበቅ አሳፋሪ እና አሸማቃቂ ንግግር የተሰናሰነ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
**የግርጌ ማስታወሻ (Foot note)  ~ እዚህ ላይ ባለፈው ለአቢይ አህመድ ጊዜ መስጠት ያስፈልጋል ያልኩትን አልረሳሁትም።
Filed in: Amharic