>

ማዕከላዊን ሳስብ፤ "ቤቱን ብቻ ሳይሆን የጨለማውን ገዳዮች ነው ማንሳት..." (አየሩሳሌም ተስፋው)

ስንያዝ በእጃችን ምንም መቀየሪያ ልብስም ሆነ ገንዘብ አልነበረም። ምርመራ እስክንጨርስም ቤተሰብ እንዳያውቅ በጥንቃቄ ነበር ፍ/ቤት አድርሰው እሚመልሱን። እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ነበር ከኮ/ር ተክላይ ጋር የተገናኘነው እሱ እሚጠይቀኝ
ማነው የመለመለሽ?
ባንቺ ስር ስንት ሰው አለ?
እኔ እምመልሰው ምንም መቀየሪያ ልብስ የለኝም በጣም እየተሰቃየሁ ነው ሴት ነኝ ብዙ ቸግር አለብኝ ቆይ ሴት ልጅ የለህም?
እንዳንቺ አይነት ልጅ የለኝም። እንኳን ሌላ ልብስ ልታገኚ እንዳንቺ ስላልሆንን ነው እንጂ የለበሽውንም አስወልቆ ራቁትሽን ነበር ማስኬድ
አብረውኝ የታሰሩትንም ሴቶችንም ማንም ልብስም ሆነ ምንም እንዳይሰጡኝ አስጠነቀቋቸው
ያለምንም ልብስ ቅያሪ 40 ቀን
ታዲያ ይህ ቤት ሲዘጋ ኮ/ር ተክላይ፣ ጥጋቡ፣ ፊሊጶስ፣ አሰፋ፣ ምንላርግልህ ፣ፅጌ………..የት ነው እሚሆኑት? እንደውም በአዲስ ሃይል ተደራጀተው እንዳይመጡ እፈራለሁ ቤቱን ብቻ ሳይሆን የጨለማውን ገዳዮች ነው ማንሳት ….
ከእስር ቤት እና እስረኞች ጉድይ ሳንወጣ
“በቂሊንጦ ዞን አንድ 370 የፖለቲካ እስረኞች የፋሲካ በዓልን በእስር ቤት ያሳልፋሉ !!
[ እስከ ረፋዱ 5፡ 50 ድረስ መነኮሳቱ በቃሊቲ እስር ቤት እንደነበሩ አውቃለሁ ]
–ይድነቃቸው ከበደ )
ቀድሞ መታሰር ያልነበረባችው እነ እስክንድር ነጋ በትላንትናው ዕለት ከእስር መፈታታቸው የሚታወቅ ነው። ለፋሲካ በዓል ከቤተሰብ እና ከወዳጅ ዘመድ ጋር አብረው ማሳለፉቸው በእጅጉ ደስ ይላል ፤ በዚሁ አጋጣሚ ከ6 ዓመት የእስር ቆይታ በኋላ በቅርብ ከእስር የተፈቱ ፖለቲኮኞች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንዲሁም ጋዜጠኞች የፋሲካ በዓልን ለመጀሪያ ጊዜ ከእስር ቤት ውጪ ያሳልፋሉ።
ይሁን እንጂ በዛሬው እለት እኔ እና ጎደኞቼ ፤ አፈወርቅ በደዊ እና ይሁን አለም በቂሊንጦ የአገዛዙ ማጎሪያ እስር ቤት በመሄድ ወንድሞቻችንን ጠይቀን ነበር። በቅርቡ እጅግ በጣም ጥቂት የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ቢፈቱም፤ በቂሊንጦ እስር ቤት ብቻ ከ370 በላይ እስረኞች እንደሚገኝ ግን ዛሬ ለማረጋገጥ ችያለሁ።  አሁን ላይ በሙስና እና “በሽብርተኝነት” የተከሰሱ እንዲሁም የእምነት አባቶችና መነኮሳትን ጨምሮ በዞን አንድ የቃሊቲ ማጎሪያ እስር ቤት በአንድ ላይ ይገኛሉ ። የእምነት አባቶችና መነኮሳት ዛሬ በቃሊቲ ማጎሪያ የክርስትና እምነት ተከታዮችን የስቅለት በዓል በማስመልከት ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓት በማስተባበር አሃይማኖታዊ ግዴታቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ ለማወቅ ችያለው። ( እኔም ከጎደኞቼ ጋር እስከ ረፋዱ 5፡ 50 ድረስ መነኮሳቱ በቃሊቲ እስር ቤት እንደነበሩ አውቃለሁ)። አሁን ላይ ተፈተዋል ስለ ሚባለው ነገር ያረጋገጥኩት ነገር ባይኖርም  ከተፈቱ ደስታው የጋራችን ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዶ/ር አብይ አህመድ በፓርላማ ኦፊሴላዊ ንግግራቸው እንዳሉት ከሆነ ” ከተለመደው የስራ ሰዓት ውጭ {ተጨማሪ ሰዓት} ሰርተው እንደሚያሰሩን ነግረውን ” ነበር ። ጽድቁ ቀርቶብኝ በውሉ በኮነነኝ እንደሚለው ያገሬ ሰው ፤ እባክዎን  በተለያዩ ማጎሪያ ቤቶች የሚገኙ የአገሬ ልጆች ! እርስዎ እንዳሉት “ጠላት ሣይሆኑ ለዚህች አገር ሁለንተናዊነት አማራጭ ሀሳብ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ” ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸዉ ።ይሁን እንጂ  የእርስዎ መንግስት በተለያየ ወቅት እያሰራ ወርቃማ የዕድሜ ዘመናቸውን እየበዘበዘ ይገኛል ። ዶ/ር አብይ፤ እርስዎ ለጊዜ የዚህን ያህል ዋጋ የሚሰጡ ከሆነ እባክዎን የእነኚህን ወገኖቻችንን ወርቃማ ጊዜ እንዲሁ እንዳይባክን በገቡት ቃል መሠረት፣ ቃልዎትን ይተገብሩ ዘንድ በተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞችን ሙሉ በሙሉ በመፍታት ከወዲሁ ጥርጊያ መንገዱን ይከፍቱ ዘንድ እንጠይቃለን
Filed in: Amharic