ወያኔ
የኦነግን ዓላማ ግን የሚያራግበዉና የሚያናፍሰዉ በግራም በቀኝም መተንፈሻ አጥሮት ተወጥሮ ያለዉ የወያኔ አገዛዝ ነዉ። ወያኔ በዚህ ሰዓት ደግሞ አደለም አንድ ኦነግ ከቻለች በሺህ የሚቆጠር ኦነግ መመስረት ትፈልጋለች። የኦረሞን ህዝብ ከሌላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ለማስገለል ስትል ሰሞኑን ደግሞ የኦነግን ባንድራ እንደነጠላ ኩታ አጣፍታ ብቅ ብላለች። ይህም የሚያሳየዉ የወያኔ ስልጣን ባለበት መቆየት የሚችለዉ ብሄርን ከብሄር ከማጋጨት በተጨማሪ አንድን ብሄር ስም የዉሸት ስም በመስጠት እንደ ተገንጣይና እንደ ብሄርተኛ በማስመሰል ለሌሎች አስመስሎ ማቅረብ ነዉ። ይህንንም ላለፉት 27አመታት ወያኔ በኦረሞ ህዝብ ላይ ሲያካህደዉ የነበረ ገሀድ እዉነታ ነዉ።
በዚህም ወያኔ በኦረሞ ብሄርተኝነት ላይ ላለፉት20 አመታት ዉጤታማ ሁኖ መዉጣት ችሏል። ዉጤታማ ከሆነባቸዉም አንዱና ዋናዉ የኦረሞን ህዝብ እንደ ብሄርተኛና እንደ ተገንጣይ አስመስሎ ለሌሎቹ ብሄሮች በማቅረብ በሌሎች ብሄሮች የኦረሞ ህዝብ እንድገለልና እንድጠላ አድርጎታል። ሁለተኛዉ መንገድ ወያኔ ዉጤታማ የሆነበት የኦረሞ ምሁራንና ፖለቲከኞችን በኦነግ ስም ወደ ማሰቃያ ካምፕ ለማጋዝና በማሰር ለመብቱ እንዳይጮህ ለማፈን ተጠቅሞበታል። ሦስተኛዉ ደግሞ የኦረሞ ወጣቶችን በኦነግ ስም በማስመሰል በጂምላ በየትምህርት ቤቱና በተለያዩ የኦረሞ ጫካወች ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ ደረስኩባቸዉ እጃቸዉን አሳልፈዉ እንድሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆናቸዉ ጀግናዉ የመከላከያ ወታደራችን ባደረሰባቸዉ ጥቃት ሊደመሰሰሱ ችለዋል በማለት ምንም ሳይፈራ በሚዲያ ለሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በመልካም ተጋድሎ ዜና ሲያሰማም አመታት ተቆጥረዋል። በሰዓቱም በኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ ተሰሚነት ስለነበረዉና የተወሰነም ድጋፍ ስላገኘ ከ1995ዓ/ም ጀምሮ በኦረሞ ህዝብ ላይ ግልጥ ጦርነት በማወጅ ለስርዓቴ ህልዉና ያሰጉኛል ያላቸዉን የኦረሞ አካባቢወች ካፀዳና ከገደለ በሗላ በተለይ ጀግናዉን
ድሮም ቢሆን ያለዉ የወያኔ ኦነግ እንጂ የኦረሞ ኦነግ የለምና ይህም ወያኔ የእራሱ ስራ መሆኑን ላልተረዳዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ጀብደኝነት እራሱን አስመስሎ አሳምኖ አቅርቧል። ከዛያችን ሰዓት ወያኔ ኦነግን ደምሰሰነዋል ኦነግ የሚባል የለም የምትለዋ ዜና ለህዝብ ይፋ ተወጣች ጀምሮ ኦነግ የሚባልም በኦረሚያ ክልል ዝር ሳይል አመታት ተቆጠሩ ነገሮችም ተቀየሩ።ያልተቀየረ ነገር ቢኖር የኦረሚያ ህዝብ ትግል ነዉ። ይህ የኦረሚያ ትግልም በትክክል የኦረሞ ህዝብ ትግል ነዉና የወያኔ እጅ ስለሌለበት ከኦረሚያ አልፎ ወደ አማራና ደቡብ ክልልም ተሸጋገረ። በተለይም በአማራ ክልል ባህር ዳርና ጎንደር የተካሄደዉ ሰላማዊ ሰልፍ የኦረሞን ህዝብ ትግል የአማራዉ ህዝብ የተረዳበትና ያመነበት ትግል ነበር። አጠቃላይ ያለፉት 4እና 5ተከታታይ አመታት ትግል የኦረሞን ማንነትና ለምን እንደሚታገል ሌሎቹ ብሄሮች የተረዱበት ትልቅ አጋጣሚ ተፈጥሯል። ይህ እድል ሊፈጠር የቻለዉ ግን የወያኔ መጠቀሚያ የሆነዉ ኦነግ በመጥፋቱና የኦረ ህዝብም የትግል አላማዉን ለሌሎቹ ብሄሮች በግልፅ ማሳወቁ ነዉ። የኦረሞ ህዝብም በየአደባባዩ የታቃዉሞ ቦታወች የሚያሰማዉ ድምፅ ”ወያኔ ይዉደም”…. ”መብታችን ይከበር” …” በገዛ ሀገራችን እንደ ሁለተኛ ዜጋ መታየታችን ይቁም!” ”እኛ የኦረሞ ህዝቦችና የቄሮ ወጣቶች የምንታገለዉ ለመገንጠልና ትልቅ ኦረሚያን ለመመስረት ሳይሆን የጋራ ሀገራችንን ኢትዮጵያን አንድነት ለማስጠበቅና በወያኔ ከፋፋይነትና ብሄርተኝነት የተስፋፋባትን ልዩነት ወደ አንድነ ለማምጣት ነዉ” በሚለዉ የሁል ግዜም መፈክራቸዉ አቋማቸዉን ገልፀዋል።
በዚህም በኦረሞ ህዝብ ሀገራዊ የትግል መፈክር የወያኔ ባላወች በየአቅጣጫዉ ተወዛወዙ ቡለናቸዉ ላላ ለድንጋጤና ለጭንቀት ወያኔወች ተጋለጡ። ምክናየቱም የኦረሞ ህዝብ ዉስጣዊ ማንነት መላዉ ኢትዮጵያኖች በግልፅ ታወቀ የኦረሞ ህዝብ በጭራሺ ከኢትዮጵያዊነቱ የሚነጥለዉን ማንኛዉንም ድርጅት እንደጥላትነት ቆጠረ በወያኔ የተነጠቀዉን ኢትዮጵያነቱን በየአደባባዩ አስመሰከረ ኦረሞ ኢትዮጵያ ያልሆነባት ሀገር በጭራሺ እንደለለችና ወደፊትም እንደማትኖር ሌሎች ብሄሮችም አወቁ።
አንድነት ሃይል ነዉ!!