>
5:13 pm - Thursday April 19, 6221

አበበ ካሴ በእስር ቤት ስለደረሰበት ግፍ ተናገረ (ጌታቸው ሽፈራው)

~ “በግብረሰዶም ወንጀል ከተፈረደባቸው እና ከአህምሮ እመምተኞች ጋር ከአንድ አመት በላይ አንድ ላይ አንድታሰር ተደርጌያለሁ”
~ በደረሰብኝ ኢ-ሰባዊ ድርጊት ኩላሊቴ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም…”
~”ከወልቃይት  ማንነት ጋር በተያያዘ አሁንም በማረሚያ ቤት ሀላፊዎች ድብደባ እየፈፀሙብኝ ነው…”
(በዳንኤል ተስፋዬ ዳንኤል ተስፋዬ ዜና ማርቆስ)
በግንቦት 7 ተከሶ 7 አመት ተፈርዶበት አ/አ ማረሚያ ቤት ቃሊቲ የሚገኘው የአበበ ካሴ በእስር ቤት በደል እየተፈፀመበት እንደሚገኝ ገልፆአል።
ከ2006 ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኘው አበበ ካሴ በቃሊቲ ማ /ቤት ከፍተኛ ስቃይና ድብደባ እንደደረሰበት ተናገረ። ከዝዋይ ማ/ቤት ወደ ቃሊቲ ከተዛወረ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በፖለቲካ አመለካከቱ ምክንያት  ሱፐር ገብረ ህይወት፣ ኦፌሰር መካሻ፣ ኦፌሰር ጥላሁን እና ሌሎችም የማረሚያ ቤቱ አመራሮች ከፍተኛ ድብደባ እንደፈፀሙበት ገልፆአል።
 ስነ ልቦና  እና አካላዊ ጉዳት እንዲደርስበት  ግበረ ሰዶም ተከሰው ከተፈረደባቸው እና የአህምሮ ህመምተኞች ለብቻቸው ከሚተሰሩበት ማቆያ እንዳሰሩትም  ተናግሯል።  “ከወልቃይት  ማንነት ጋር በተያያዘ እዚህ ሆነህ ወጣቶች እንዲደራጁ፣ እንዲያምፁ፣ በወልቃይት ጉዳይ ህዝብ አቋም  እንዲይዝ መልህክት አስተላልፈሃል” በሚል ድብደባ ተፈፅሞብኛል ብሏል።
“እስር ቤት ውስጥ በደረሰበት  ድብደባ ኩላሊቴ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶብኛል። ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም” ብሏል።  ይህን መረጃ ያጠናቀረው ዳንኤል ተስፋየ አበበ ከፍተኛ የሆነ የወገብ ህመም እና ድካም እንዳለበት  መታዘብ ችሏል።
 በሌላ ክስ 20 አመት ተፋርዶበት ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍ/ቤት ቅጣቱ ተፈፃሚ እንዲሆን ትህዛዝ  ለቃሊቲ ማ/ቤት መሰጠቱን አበበ ገልጿል። አበበ ካሴ በማዕከላዊ
 ወንጀል ምርመራ በደረሰበት ድብደባ እና ስቃይ 20 የእግሩ እና የእጁ ጥፍሮቹ ሙሉ በሙሉ መነቀላቸው፣  ብልቱ መኮላሸቱ፣  በኤሌክትሪክ ንዝረት በተፈፀመበት ግርፋት  ለ11 ወራት ያህል  አንድ ጎኑ  ደንዝዞ እንደነበር በዚህም ምክንያት የእግሩ ጡንቻዎች መሸማቀቃቸው መግለፁ ይታወሳል።
Filed in: Amharic