>
5:13 pm - Saturday April 19, 2442

“መይሳው ካሳ” (እሸቱ ጥሩነህ)

ምስሉን የሳሉት ዕውቁ ሰዓሊ፣እሸቱ ጥሩነህ ናቸው፡፡ እንደ ስዩም ወልደ ምስክርነት በመጀመሪያ  የተሳለውም ሞስኮ ላይ ነው፡፡ እሸቱ ጥሩነህ፣ሰባት ዓመት ገደማ በሞስኮ ለከፍተኛ ትምህርት ቆይተው ለመመረቂያ ያዘጋጁት ነው፡፡ ርእሱም  “መይሳው ካሳ” ነው፡፡ በዚያ የተሠራው 2 ሜትር ከ40 ሴንቲ ሜትር በ3 ሜትር ሆኖ ነው፡፡ ግዙፍ ስእል ነው፡፡
ስእሉ በርካታ ሕዝብ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ያሳያል፡፡በምስሉ ፊት ለፊት ነጻ ስፍራ ሆኖ ነገር ግን የሕዝብ ጥላ ሰፍሮበታል፡፡ በመካከል ላይ ደግሞ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ያሳያል፡፡ ጎልተው የሚታዩት ግን የመይሳው ልጅ ናቸው፡፡ ፈረሳቸውም ቅብጥብጥ መሆኑ ያስታውቃል፡፡
አብረው ያሉት ሁሉም ሰዎች በአንድነት የሚጓዙ፣ለአንድ ዓላማ መሰለፋቸውንም ያሳያል፡፡ ጦረኛውም፣አዝማሪውም፣መለከት ነፊውም ሁሉም፡፡ ከጀርባው ያለው ቦታ ላይ ደማቅ እና ወርቃማ ብርሃን ሲኖር ሰዎቹ ላይ ግን የደበዘዘ ነው፡፡ ጽልመትን፣የሚያጋጥማቸውን ዕድል ለማሳየት ነው፡፡
 ከመይሳው ልጅ በፊት ለፊት ያለው ደግሞ የደመና ጥላ ነው፡፡ የመይሳውን ልጅ ሁኔታው እንደከበደበት ለመግለጽ ይመስላል፡፡ እንደውም የሠራዊቱን ጉዞም የሚገታ መስሎ ነው የተሳለው፡፡ የመይሳው ልጅን ፍጻሜ ለማሳየት የተሳለ ነው፡፡
ስለ ስእሉ የቀረበው ገለጻ የስዩም ወልዴ እንጂ የእኔ አይደለም፡፡ ሰፋ ያለ ገለጻ ስለሆነ በአጭሩ ብቻ የማስቀመጥ ሥራ ነው እኔ ያደረኩት!
ምንጭ፡– ስዩም ወልዴ፣”የቴዎድሮስ ገጽታ በታሪካዊ አሳሳል ውስጥ”፤ ውስተ Taddese Beyene et al(eds), “Kasa and Kasa: Papers on the Lives,Times and Images of Tewodros II and Yohannes IV”, Addis Ababa,1990, ከገጽ 157-172፡፡
Filed in: Amharic