>

የፍቅርና የአክብሮት ምላሽ  (አርቲስት መሰረት መብራቴ)

የጥበብ ስራን ከማየትና ከማድነቅ በላይ ለተጠባቢው ፍቅርና አክብሮትን የሚለግሰው ውድ ህዝብ አሁንም የጋሽ ፍቃዱን መታመም ከሰማበት ጊዜ ጀምሮ ያሳየው ወደር የሌለው የፍቅር ምላሽ እጅግ የሚያስደስት ነው:: በመላው አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ” ለወገን ደራሽ ወገን ነው” በሚል  ከልብ በመነጨ ፍቅር ወገናዊነታቸውን በተግባር አያሳዩ ነው:: በፀሎት ከማሰብ ጀምሮ ኩላሊታችንን መለገስ እንፈልጋለን የሚሉ እና በሀሳብም በገንዘብም የደገፉ በርካቶች ናቸው አሁንም አለሁ ባይነታችሁ ይቀጥል:: እግዚአብሔር ያክብርልን::
ያሰብነው ተሳክቶ የምንወደው እንቁ አርቲስታችን በሙሉ ጤንነት በሚወደው መድረክ ላይ ቆሞ ለማየት ያብቃን:: እግዚአብሔር አምላክ በምህረት እንዲጎበኘው ሁልጊዜም በፀሎታችሁ አስቡት:: በገንዘብ ለምትደግፋ:-በሀገር ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000239345488
በውጭ ሀገራት ለምትኖሩ https://www.gofundme.com/help-save-fikadu-tmariam039s-life
Filed in: Amharic