>
5:13 pm - Monday April 20, 9485

የታሰቡት ሁለቱ የመንግስት ለውጥ አማራጮች  (ሚሊዮን አየለች)

አሁን አሁን እየወጡ ያሉት መረጃዎች በህውሀት የሚመራውን መንግስት ለመጠል ሁለት አይነት መንገድ መታቀዱን አንዳንድ ምንጮች እየዘገቡ ይገኛል 
1የታሰበና የታቀደ ግን በአጋጣሚ የሆነ መፈንቅለ መንግስት ማድረግ
2የባለ አደራ መንግስት አቋቁሞ ህዝቡ ከተረጋጋ በኋላ አስቸኳይ ምርጫ ማድረግ
1.የመጀመርያውና በስፋት አሁን ላይ እየተሰማ ያለው ወሬ መፈንቅለ መንግስት በሚመስል የስልጣን ሽግሽግ የኢትዮጵያን ህዝብ ዳግመኛ ለማታለል ከህውሀት አመራሮች የመጣ ተልካሻ ሀሳብ ይመስለኛል ኢትዮጵያውያን አሁን የሚፈልጉት በመላው ደረጃ ሙሉ እና ስር ነቀል ሊባል በሚችል ሁኔታ ኢትዮጵያ ከዚህ አረመኔያዊ ተግባር አገዛዝ ሙሉ በሙሉ ነጻ ሊያደርጋት የሚችል መፍትሄ ነው የመፈንቅለ መንግስት ጠንሳሽና አራማጆችም በዚህ በመፈንቅለ መንግስት ሰበብ ህዝብ ላይ የሰሩትን አረመኔያዊ ግፍ ሊሸፍንላቸው የሚችል አሻንኩሊት መንግስት ከበላይ በማስቀመጥ እነሱ ለ26 ዓመታት ሀገሪቷን ዘርፈው ያካበቱትን ሀብት በስደት ወደተለያዩ ሀገራት በመሄድ ለመጠቀምና በህግ እንዳይጠየቁ የኢትዮጵያውያን ከህፃን እስከ አዛውንት የፈሰሰውን ደም አድበስብሶ ለማለፍ በመፈለጋቸው ነው፡፡
መፈንቅለ መንግስቱ ሲታሰብ መፈንቅለ መንግስቱ አድራጊው ማን ነው? መፈንቅለ መንግስቱንስ የሚደግፉት እነማን ናቸው? የመፈንቅለ መንግስቱ ትክክለኛ አቅጣጫ ምንድን ላይ ያነጣጠረ ነው? በመፈንቅለ መንግስቱ የሚጠቀመው ማን ነው? ህዝቡስ መፈንቅለ መንግስቱን ይደግፈዋል ወይ (በህዝቡ ዘንድ ሙሉ ይሁንታ አግኘቷል ወይ)?… የሚሉትንና ለሎች ወሳኝ ጥያቂዎችን አስቀድመን ማንሳት ይጠበቅብናል፡፡
የዚህ መፈንቅለ መንግስት ዋና አቀንቃኝ ህውሀት እንደሆነ ቀድሜ እንደገለፅኩት ሁሉ የአሜሪካ እጅም እንዳለበት በአሜሪካ ሀይሎች መፈንቅለ መንግስቱ እንደሚቀነባበር ገሀድ እየወጣ ይገኛል ይህ አይነት አካሄድ ደግሞ ለነፃነቱ ብሎ ደረቱን ለጥይት እየሰጠ ላለው ሰው የብስ ንቀት ነው ፡፡ ያልተቆራረሰ ያልተሸራረፈ ነጻነት በነጻነት ማሰብ እንድንችል በነፃነት እኩል ማናቸውንም ላይ ሊዳኝ የሚችልበት የህግ ስርአት በቋንቋ በብሔር የማይዳኝበት በማንነቱና በኢትዮጵያዊነት ብቻ ሊዳኝበት የሚችልበት አግባብነት ያለው ፍትህ ባጠቃላይ ለሁሉ በእኩል የምትኖር አንዲት ኢትዮጵያን መፍጠር ነው የሚፈልገው ለዚህም ነው በአደባባይ ወጥቶ አሻፈረኝ የሄ አይነት አገዛዝ ይብቃኝ ብሎ ባዶ እጁን ከጥይት ጋር እየተፋለመ የሚገኘው፡፡
የህውሀት አገዛዝ በኢትዮጵያ ላይ ግብአተ መሪቱ እስካልተፈፀመ ድረስና በዚህ አረመኔያዊ መንግስት ስር ያሉ የስርአቱ ዋነኛ አቀንቃኞችና ጀሌዎቻቸው ተላልፈው ለፍርድ እስካልቀረቡ ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ መቺም ቢሆን እንቅልፉን አይተኛም፡፡ ወንድሙን በጠራራ ፀሀይ አሳዶ የገደለም አሳድዶ እንዲገል ያደረገ አዛዥም ሁለቱም በእኩል ፍርድ ቤት ቀርበው ተገቢውን ቅጣት ሲያገኝና ፍትህ ከእነዚህ አንባገነኖች የበላይ ስትሆን ሲያይ ያኔ ነው ህዝቡ የሚያርፈው ያኔ ነው ለፍትህ ሲሉ ደማቸውን የገበሩ እህት ወንድሞቼ ከፍ ባለ የታሪክ መዝገብ ላይ የምፅፍው ፡፡
ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገውን ምዕራፍ ለማየት በእነዚህ ሀይሎች እየተተገበረ ያለውን ተልካሻ ማታለያ መፈንቅለ መንግስት አይቀበለውም በዚህ በኩል ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ነቅተህ ጠብቅ እላለሁ፡፡
2.ሁለተኛውና በከፊልም ቢሆን አሁን ላለችው ኢትዮጵያ መፍትሔ ይሆናታል ተብሎ የተገመተው የባለ አደራ መንግስት ማቋቋም ላይ ነው
ይሄም ቢሆን በትክክልና በግልፅ በሆነ መልኩ ካልተሰራበት አደጋው መልሶ የከፋ ይሆናል ቀደም ብዬ እንዳልኩት የሚፈለገው ያልተሸራረፈ ነፃነት ዳግመኛ ኢትዮጵያ ወደ እንደዚህ አይነት አስከፊ ስርአት እንዳትመለስና ህዝቦቿ እኩል ተጠቃሚ ሆነው ሁሉንም ህዝቦች በእከልነት የምታኖር ኢትዮጵያን ነው፡፡
ይሄ ደግሞ በአሜሪካ መንግስት የሚደረግ የሽግግር መንግስት ምስረታ በእኔ እይታ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነው፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ በተለይ በአፍሪቃ ቀንድ በኩል ያላት ኢትዮጵያን ማዕከል አድርጎ መላው ምስራቅ አፍቃን ለመቆጣጠር የሚያስችላትን መዋቅር የዘረጋች ሀገር ናት ስለዚህ ኢትዮጵያ በአሜሪካ አይን ፍፁም የተረጋጋች እና ሰላማዊ ሆና እንድትኖር አትፈልግም እንዲሁ ደግሞ እጅግ የከፋ ብጥብጥ በሀገሪቷ ላይ እንዲኖርም አትፈልግም ሁለቱም ምክንቶቿ ከራሷ ጥቅም አንፃር የተቃኘ ነው፡፡
ፍፁም የተረጋጋች እና ሰላማዊ ኢትዮጵያ ከተፈጠረች ኢትዮጵያ አይደለም ከአፍቃ ከዓለምም በኢኮኖሚም በጦር ኃይሏ በአጠቃላይ በፖለቲካ ሀይሏ ቀዳሚ እንደነበረችው ሁሉ ገናናና የዓለምን የሀይል ሚዛን መልሳ እንደምትቆጣጠር ባለ ሙሉ እምነት ስላላቸው ያ እንዲሆን አይፈልጉም በመሰረቱ ይህንን አይነት አመለካከት የሚያቀነቅኑት አሜሪካ ብቻ ሳትሆን አውሮጳ እና አንዳንድ የሩቅ ምስራቅና የላቲን ሀገራት ጭምር ናቸው፡፡
ሌላውና በተጨማሪ በኢትዮጵያ ውስጥ የለየለት ብጥብጥ እንዳይፈጠር የማትፈልገው ዋንኛው ምክያት ቀደም ብዬ ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት የምስራቅ አፍሪቃን ቦታ ለመቆጣጠርና ሽብርተኞችን ለማን ሁነኛ ስፍራዋ ኢትዮጵያ ስለሆነች ነው ይህ ሳይሆን ቢቀር ኢትዮጵያ በሰላም ማጣት የምትናጥ ከሆነ ዓለምን ያሰጋው ሽብርተኝነት በከፍተኛ ደረጃ ተንሰራፍቶ እራሷ አሜሪካንን ጉሮሮዋን እስከ ማነቅ እንደሚደርስ ታውቀዋለች፡፡
በዚህና በተለያዩ ምክንያቶች የአሜሪካን መንግስት እጅ ወደ ኢትዮጵያ ውስጥ ስር ሰዶ መግባትን ይፈልገዋል፡፡
እኔ ግን የምለው አሁንም የኢትዮጵያውያን ትልልቅ የህዝብ የፖለቲካ ድርጅች ከሚመስላቸው ከሚመስላቸው ጋር የፖለቲካ ውህደት ፈጥረው ከራሳቸው በፊት የኢትዮጵያ- ህዝብ በማስቀደም ዳግመኛ ወደ እንደዚህ አይነት ሰው በላ አውሬ ስርአት እንዳትገባ ታሪካዊ ስራ ሰርተው ለትውልድ ቢያልፉ መልካም ይሆና የማንም ሀገር ጣልቃ ገብነት የሌለባት ታላቂቷ ኢትዮጵያን ለመገንባት አሁን ያሉት የፖለቲካ ድርጅች ታላቅ ታሪካዊ አደራ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይጠብቃት
Filed in: Amharic