>

በስሜ  እየተሰራጨ ያለውን የተሳሳተ መረጃ በተመለከተ ይሕንን ማስታወሻ በድጋሚ ለመጻፍ ተገደጂያለሁ፤ (ሲሳይ አጌና)

 በስሜ እና በምስሌ በፌስ ቡክ እየተሰራጨ ያለው  ውዥንብር የኢሳት ባልደርባው ሲሳይ አጌና አለመሆኑን በድጋሚ ማረጋገጥ እወዳለሁ።
    በስሜ የሚጽፈው ግለሰብ የመብት ተሟጋቾችን እንዲሁም ታዋቂ አርቲስቶችን በተመለከተ የተዛቡ ዜናዎችን እንዲሁም ምኞቱን ሲገልጽ ቆይቷል።ታዋቂውን ኢትዮጵያዊ ምሁር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምን፣ዝነኛውን የሙዚቃ ሰው አሊ ብራን ፣አክቲቪስት ታማኝ በየነን  በተከታታይ ሞተዋል  የሚል ውዥንብር አሰራጭቷል።የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት  በሳኡዲ አረቢያ ሞት ተፈረደባቸው በማለትም ማህበርሰቡን አስደንግጧል።
ይህ ሁሉ ልብ ወለድ ድርሰት የፌስቡክ ተከታታዮች የግለሰቡን ማንነት እንዲያውቁ በቂ ቢሆንም፣ ዛሬም በልበወልዱ ዜና የሚሳቡ እና የሚያስተጋቡ መታየታቸው ያሳዝናል። ግለስቡ ወይንም ቡድኑ በዛሬው ዕለት ደግሞ ታዋቂው የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ  አጫሉ ሁንዴ ታስረ ሲል ጽፏል።በኔ ግምት ብናስረው ምን ይከተላል የሚለውን የሕዝቡን ስሜት ለመለካት ከሕወሕት ሰፈር የተለቀቀ መረጃም ይመስለኛል።ይህ ደግሞ  የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጨው ግለሰብ ወይንም ቡድኑ እየሰሩ ያሉት ሰዎችን በማስደንገጥ ለመደሰት ወይንም ለመዝናናት  አለመሆኑን በተወሰነ ደረጃም ይፈነጥቃል።ከህወሃት እና ደጋፊዎቹ ሰፈር ሞቱ የሚል ልብ ወለድ መረጃ  ሲጸፍ አለመታየቱም ግለሰቡ ወይንም ቡድኑ  ሰልፉ ከየት እንደሆነም ተጨማሪ ምልክት ይሰጣል።
በአጭሩ የኢሳት ባልደረባው ሲሳይ አጌና እስከዛሬዋ  ዕለት ድረስ አንድም መረጃ በስሜ በፌስ ቡክ አለመውጣቱን እያረጋገጥኩ፣በስሜ የሚወጡትን መረጃዎች ለመግታት ወይንም የእኔ አለመሆኑን ለማረጋግጥ የራሴን ፌስ ቡክ አክቲቭ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ስለተመከርኩ  ይህንን ለማድረግ ተገድጄያለሁ።ይህንን በማሰራጨት ወዥንብሩን በመቅረፍ እንድትተባበሩኝ በአክብሮት ጠይቃለሁ።
Filed in: Amharic