>

ባለ ሁለት ከንቲባዋ ከተማ (ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ)

አዲስ አበባ ሁለት ስውር ከንቲባዎች አሏት። ሁለቱም ከትግራይ የመጡ የአዲሳአባን ህዝብ በጠላትነት የሚያዪ ምስለኔዎች ናቸው። አንደኛው ሐይሌ ፍስሃ ( የአርከበ የስጋ ዘመድ)ሲባል የማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆን የመዲናይቱ አገልግሎት ተቋማትና የመሬት ባለቤት ነው። ሁለተኛው ስዉሩ ከንቲባ ተጋዳላይ ተወልደ ገ/ፃድቃን የሚባል ሲሆን የአዲሳአባ ኢህአዴግ ቢሮ ሐላፊ በመሆን የፀጥታና ስለላ ስራዎችን በበላይነት የሚጠረንፍ ነው።
ዛሬ ተጋዳላይ ተወልደ በፓርቲው ድረ ገፅ ላይ ወጥቶ፣
” የከተማችን ነዋሪዎች የፀረ ሰላም ሀይሎችን ጥሪ ሊቀበል አልቻለም። የከተማችን ህዝብ ከብጥብጥ የሚገኝ ጥቅም እንደሌለ ከልምዱ ያውቀዋል” ይለናል።
ተጋዳላዩ በተዘዋዋሪ እየነገረን ያለው፣
# ከመዲናይቱ ውጭ የሚኖረውና ህዝባዊ እምቢተኝነት ያነሳው ህዝብ “የፀረ ሰላም ሀይሎች” ጥሪ ይቀበላል።
# የአዲሳአባ ህዝብ ከዚህ በፊት ይበጠብጥ ነበር። በሌላ አነጋገር “የፀረ ሰላም ሀይሎችን” ጥሪ ይቀበል ነበር። አሁን ግን ከልምዱ ተምሮ አይበጠብጥም።
ንግግሩን በደንብ እንተርጉመው ካልን በሁለት ልንከፍለው እንችላለን፤ አንድምታ ማለት ነው፡፡
አንድም  ፈሪዎች ናቸው፤ አቋመ ቢስ ናቸው፤ የኢትዮጵያዊነት ወኔ ከውስጣቸው ተሰልቧል፤ ትግሉ እንዳይሰምር እንቅፋት ሆነዋል፤ እንተማመንባቸዋለን፤  ማለት ሲሆን፡፡
ሁለተኛው ደግሞ የተለያዩ ክልል ያሉትን ህዝቦች ወደ ልዩ ልዩ ክልል እንዲሰፍሩ ስናደርግ፤ የትግራይ ሰፋሪዎች በብዛት የሰፈሩት አዲስ አበባ ስለሆነ፤ እንደ ቅኝ ግዛት መዲና ናት፤ አዲሳቤ ደግሞ የተደገመበት ይመስል የመጣውን  ሁሉ እናቴን ያገባ አባቴ ነው እያለ ድራማ እየሰራና እያየ  ይኖራል፤ አዲስ አበባ ዙርያ ተዘግቷል ምንም እንቅስቃሴ የለም ሲባል ፐ እያለ ነው ሚኖረው፤ እኛ ደግሞ ኦሮሞ ሊወርህ ነው ስንለው፤ ሚመርጠውን አጥቶ ፈዟል ፡፡ ስለዚህ ምንም አያመጣም ማለት ነው፡፡
Filed in: Amharic