>

አቶ ለማና ቡድኑን ህወሃት ከሳለላቸው ቢላ የምናድናቸው እኛ ነን እና ከጎናቸው እንቁም!!! (ብርሀነ መስቀል አበበ)

በህገወጡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሽፋን ህወሃት በኦሮሞ ህዝብ ላይ የከፈተው ጦርነትና ሽብር ዋነኛ አላማ የፕረዚደንት ለማን ቡድን ለመምታትና እነለማ በኦሮሚያ ፓሊስ፣ በOBN እና ኦህዲድን ከህወሃት ዕቃነት አውጥተው የኦሮሞ ህዝብ ድርጅት ለማድረግ የጀመሩትን ውጥን ስራዎች ለማፍረስ ነው። ለዚህ ደግሞ ህወሃት ያሰማራቸው ጀሌዎች ሰዋችን በገንዘብ መግዛትን ጨምሮ ከፍተኛ የማስፈራራት እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል።
 ስለዚህ የኦሮሞ ህዝቡ ከአቶ ለማ መገርሳና እርሱ ከሚመራው ቡድን ጎን በመሰለፍ የትኛውንም የህወሃት ጥቃት መከላከልና የህወሃትን ሴራ ማፍረስ መቻል አለበት። ህወሃት የኦሮሞ መሪዎችን እንደፈለገ የሚገልበት፣የሚያስርበት እና ድርጅቶቻቸውን በዘፈቀደ የሚያፈርስበት ዘመን እንዳአበቃ ማወቅ አለበት።ከዚህ በኋላ በዚያ መንገድ ለመሄድ ቢሞክ የኦሮሞ ህዝብ በህወሃት የኢኮኖሚ፣የፓለቲካና የፀጥታ አውታራሮች ላይ አይቀጡ ቅጣት እንደሚወስድ ህወሃት መገንዘብ አለበት።
እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ህወሃት የሰው ልጆች ሲገል፣ ለህይወት ዋጋ የማይሰጥና በሌብነት ያጠራቀመው ኃብቱ በእሳት ሲጋይ ብቻ የሚደነግጥ ቡድን መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ያለፉት ሶስት ዓመታት ትግል በግልፅ አሳይቷል። ስለዚህ ህወሃትን ለማሸነፍ የኢኮኖሚ መሰረታቸውን ንዶ ማክሰር የህዝባዊ ትግሉ ግንባር ቀደም ስልት መሆን አለበት።
 የህዝብ ትግል በህወሃት እንዳይቀለበስ የኦሮሞ ወታደሮችና የፀጥታ ሰዎች በዚህ ቁርጥ ጊዜ ከኦሮሞ ህዝብና መሪዎች ጋር እንዲቆሙ ለማድረግ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው።
የኦሮሞ ተቃዋሚ የፓለቲካ ድርጅቶችም በማስተዋልና ስትራቴጂ ጉድለት እነለማ መገርሳን ለማጥፈት በተጀመረው ጦርነት የህወሃት መሣሪያ እንዳይሆኑ ከወዲሁ አቋማቸውን ግልፅ አድርገው ከነአቶ ለማ መገርሳ ቡድን ጋር መቆም አለባቸው። ህወሃት የእነለማ መገርሳን ቡድን አጥፍቶ የኦሮሞ ህዝብን ከኦሮሞ ተቋዋሚ የፓላቲካ ድርጅቶች ጋር አደርጋለው በሚል የተለመደ የህወሃት ሸፍጥ መደለል እንደማይችል ከወዲሁ መገንዘብ አለበት።
የኦሮሞ ህዝብና ቄሮም በእነ አቶ ለማ መገርሳ ዙሪያ ህወሃትና ጀሌዎቹ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴዎች በአይነ ቁራኛ መከታተልና የህወሃት ውጥኖችን በማፍረስ አፋጣኝ እርምጃዎች መውሰድ መጀመር አለበት።
 በኦሮሚያ ፓሊስ፣ በ OBN እና በተራማጅ የኦህዲድ አባለት ላይ የህወሃት ታጣቂዎችና በኦሮሞ ስም የሚነግዱ ባንዳዎች የሚያካሄዱትን ጥቃት የኦሮሞ ህዝብ መከላከልና ባንዳዎቹን ከውስጡ ነቅሎ ማጥፋት አለበት።
በተመሳሳይ ሁኔታ የፕረዚደንት ለማ መገርሳ ቡድን ህወሃት በሳለላችላቸው ቢላዎ ከመታረድ የሚያድናቸው ብቸኛ ኃይል የኦሮሞ ህዝብ ብቻ መሆኑን ተገንዝበው ከህዝባቸው ጋር የለት ተዕለት ግንኙነቶቻቸውን ማጠናከርና አመራር መስጠቱን አጠናክረው መቀጠል አለባቸው።
ለዚህ ደግሞ ከመጋረጃ ጀርባ ህወሃት ከሚሸርባቸው የወንጀልና የክህደት ሴራ ሜዳ ወጥተው በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ እየተፈጠረ ያለውን የአመራር ክፍተት በፍጥነት በመሙላት የህዝብ ሰላማዊ የትግል መሪዎችና የለውጥ የኃዋሪያነት ሚናቸውን በግልፅ አመራር በመስጠት መወጣት አለባቸው።
የጠቅላይ ሚኒስትር ቦታውን በተመለከተ በህወሃት በኩል የሚመጣ ሹመት ውርደት እንጂ ክብር አንደማያመጣ መገንዝብ በጣም አስፈላጊ ነው። ስልጣን ከህዝብ ሲሆን ብቻ ነው ክብር።
 ስለዚህ የህወሃት የአሻንጉሊት የስልጣን ወንበሮች ተፈርታችሁና ተከብራችሁ ስለሚገባችሁ ስትረከቡት ብቻ የሰላማዊ ሽግግሩ መሣሪያ ሊሆን እንደሚችል መረዳት አለባችሁ። ያ ከልሆነ የህዝብ ትግል ማዘናጊያ ወጥመድ እንጂ የሥልጣን ወንበር አይሆንም። በክብር ያልተቀባላችሁትን ወንበር በውርደት መልቀቅም ይመጣል።
በመሆኑም የጠቅላይ ሚኒስትር ወንበሯ ስምና ወጥመድ ብቻ የሚትሆን ከሆነ ከህወሃት እጩዎች አንዱ( አቶ ደመቀ መኮንን ወይም ሽፈራው ሹጉጤ) የአሻንጉሊት ወንበሩን በቶሎ ቢረከቡ ስረዓቱን ለማፈረረስ የተጀመረውን ህዝባዊ አመፅ በመቶ እጥፍ እንደሚያፋጥነው በመረዳት ከዙሪያቸው ዞር በሉ። እየሰጠመ ያለውን የህወሃት ጀልባ አትሳፈሩ። የኦሮሞ ህዝብም መሪዎቹን ከጠላት ጅቦች ጋር እንዳይበላ ይጠንቀቅ።
Filed in: Amharic