>
5:13 pm - Monday April 18, 4185

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን'' 346 ድምፅ ውድቅ አድርጎታል። (ስዩም ተሾመ)

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣውን “የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ” ውድቅ አድርጎታል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 547 ወንበሮች ያሉት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 8 ወንበሮች ተጓድለዋል።በዛሬው ስብሰባ ላይ የተገኙት 441 የምክር ቤት አባላት የቀረበውን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በ346 ድጋፍ፣ 88 ተቃውሞ እና 7 ድምፀ-ተአቅቦ ውድቅ አድርገውታል። በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 93.2(ሀ) መሰረት “አዋጁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለት ሦስተኛ ድምፅ ተቀባይነት ካላገኘ ወዲያውኑ ይሻራል” ይላል። በዚህ መሰረት የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ የሁለት ሦስተኛ ተቀባይነት የሚያገኘው 365 ድምፅ ድጋፍ ሲያገኝ ነው። ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተገኙት ውስጥ EBC፣ OBN እና VOA ይገኙበታል። እነዚህ የሚዲያ አውታሮች አዋጁ ድጋፍ ያገኘው በ346 ተወካዮች ብቻ እንደሆነ በመቅረፀ ድምፃቸው አስቀርተውታል። ሆኖም ግን፣ የምክር ቤቱ ሬጅስትራር በጓሮ በኩል መጥቶ አዋጁ የ395 ድምፅ ድጋፍ እንዳገኘ ተናግሯል። በሀገር ሕልውና ላይ የሚተላለፍ እንዲህ ያለ ውሳኔ እንዴት ሆኖ ነው የቁጥር ስህተት የሚሆነው። የፈጣሪ ያለህ….

Filed in: Amharic