>
5:13 pm - Thursday April 19, 5534

እስኪ እንነጋገር አለ ብዙ ነገር (አበባየሁ ደመቀ)

በሚቀጥለው ሳምንት ኢህአዴግ ሊቀመንበሩን ይመርጣል፡፡አባል ድርጅቶቹ ወኪሎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡ኦህዴድ በግልፅ እና በዴሞክራሲያዊ መንገድ ከቲም ለማ ውስጥ ሌ/ኮ ዶ/ር አብይ አህመድን መርጧል፡፡ከአብይ ምርጫም በኃላ ክቡር አቶ ለማ መገርሳ የኢትዮጵያን ህዝብ ያረካ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ቲም ለማ የመወከሉን ስራ በስኬት አጠናቋል፡፡ብአዴን ስብሰባውን በሰላም ቢጨርስም ጎመን በጤና በሚል ቢሂል አመራሩን ሳያጠሩ እርስ በርሳቸው ሳይነካኩ መግለጫ በመስጠት ስብሰባው ተጠናቋል፡፡ለኢህአዴግ  ሊቀመንበርነት የወከሉትን ሰው በይፋ ባይነግሩንም የብአዴን ሊቀመንበር የሆነውን ደመቀ መኮንን ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡ደቡቦች ሽፈራው ሽጉጤን ወይንም ሲራጅ ፈርጌሳን ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡
እስኪ እንነጋገር
አለ ብዙ ነገር
ለዶ/ር አብይ አህመድ ኮፍያችንን ከፍ ስናደርግ ብሄርተኛ እንደሆንን፣በብቃት እንደማናምን፣ኦሮሞ በስልጣን ተጎድቷል ብለን እንደምናቀነቅን(ኦሮሞ ከሚሊኒክ ዘመን ጀምሮ ያገኘውን ስልጣን እያብራሩ ሊያስረዲን የምከሩም አሉ)ባጠቃላይ ዛሬም በኛ አመለካከት ላይ አመድ ለመከመር የሚዳክሩ አልጠፋም፡፡መብታቸው ነ፡ይህች ጎንበስ ጎንበስ እቃ ለማንሳት መሆኑ ይገባናል፡፡ግን እንዲስተዋል የምንፈልገው ነጥብ
1)አሁን ባለው የውክልና አሰራር ሁሉም አባል ፓርቲዎች ምርጥ የተባለውን ሰዋቸውን ነው የሚያቀርቡት(የውጭ ተዕፅኖ የለባቸውም ብለን ካሰብን)::ከሁሉም ዶርጅቶች ምርጦች ውስጥ ምርጥ የሆነው ማነው?ብለን አስበን ዶ/ር አብይ ብንል ጎሰኛ ያሰኛል?
2ኛ)ተመራጩ ጠቅላይ ሚኒስተር አሁን ያለውን ህዝባዊ እንቅስቃሴ በአግባቡ ህዝብን እያግባባ የህዝብ ጥያቄ ሊመለስበት ወደሚችልበት ሂደት አቅጣጫ የሚመራው የቲም ለማ አባል የሆነውነው ዶ/ር አብይ ወይንስ ደመቀ መኮንን ወይም ሽፈራው ሽጉጤ ነው?ማነው ሰፊ መሀበራዊ ድጋፍ ያለው የሚለውን ጥያቄ መጠየቅ በቂ ይመስለኛል
3ኛ)በብቃት ከሄድን ከአባል ድርጅቶቹ ወኪሎች ውስጥ ማነው ብቁ?ቲም ለማ ብቃቱን በተለያየ ሁኔታ አላስመሰከረምን?ከመአከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በኃላ የቲም ለማ መግለጫ ከሌሎቹ ጋር ሲወዳደር የቱ ተስፋ ሰጪ ነው?
4)የኢትዮጵያ ህዝብ ቲም ለማን አንፃራዊ በሆነ ሁኔታ ይቀበላል ወይንስ አይቀበልም?
5ኛ)ከወኪሎቹ ውስጥ ማነው የወከለውን ክልል ህዝባዊ ድጋፍ ያለው?ቄሮ ቲም ለማን የሚደግፈውን ያህል ፋኖ ደመቀን ይደግፋል?ለማንኛው ጉዳይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥሪ ቢያቀርቡ በአንፃራዊ መልኩ ከህዝቡ ቀና ምላሽ የሚያገኘው ቲም ለማ ወይንስ ደመቀ?
6ኛ)በብሄር ከሄድን በ27 የአውራው የስልጣን ዘመን የጠቅላይና የም/ጠቅላይ ቦታ የየትኛው ብሄር ነው?ፀሀይ የሞቀው ሀገር ያወቀው ሀቅ ነው?ታድያ ፍትሀዊነቱን አይተን አብይ አብይ ስንል ጎሰኞች ጎሰኞች የምትሉን ሰዎች ራሳችሁ ጎሰኞች መሆናችሁ አይደለምን?ማንን እንበል እስኪ ንገሩን?ደመቀ እንዳንል እስከዛሬ ምን አሳየን?ሽፈራውን እንዳንል ጥያቄ አለን?
7)ብቃትን ካነሳን እንደዶ/ር አብይ ብቁ የለም ከእጩዎቹ፡፡ኢንሳ ይመስክር፡፡ቲም ለማ ይመስክር
በመሆኑም መከራከርያ ነጥብ ይቅረብ፡፡በየትኛውም መስፈርት የቲም ለማ አባል የሆነው ዶ/ር አብይ አህመድ ወደአራት ኪሎ ቢገባ ትክክልና ፍትሀዊ ነው፡፡እንደኩፍኝ እንዲወጣላችሁ ሳልተረጉምላችሁ አንድ ነገር ልበል
Araat kiilof nutu  aane
አራት ኪሎፍ ኑቱ አኔ
Filed in: Amharic